ጌታ የበጎ አድራጎት ድርጅት
GeTa Charitable Organization

የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ

የበጎ አድራጎት ድርጅታችን ዓላማውንና ግቡን መሠረት አድርጎ ለሚያኪያሂዳቸው እርምጃ ሁሉ ጠቃሚ የሚሆን ሰነድ

ጌታ የበጎ አድራጎት ድርጅት ያዘጋጀው ይህ ስትራቴጂክ እቅድ ዓላማውን፣ ግቡን፣ ተደራሽ የሚያደርጋቸውን የሕብረተሰብ ክፍል ጥቅም፣ የሚያከናውናቸውን ተግባራት፣ የሚቆጣጠር እና ለሥራ የሚያሰልፋቸውን አመራሮች በተቀናጀ መልኩ ወደ ግቡ እንዲደርሱ የሚገኘውንም ማናቸውም ሀብት ባለማባከን በተገቢው ቦታ እንዲውል ይመራል፡፡

ግንቦት 12 ቀን 2013 ዓ.ም
ጌታ የበጎ አድራጎት ድርጅት
GeTa Charitable Organization

የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ

ተልእኮ

ጤናማ ቤተሰብ፣ የትዳር እውቀት በጋብቻ ምሥረታ ላይ እንዲኖር፣ ፍቺ እንዲቀንስ፣ የቤተሰብ መበተን ያሚያስከትለውን ጉዳት ማስቀረት፣ የጎዳና ተዳዳሪ ወጣት ምንጭ ለማድረቅ፣ ወላጅ አልባ ወይም ወላጅ ላላቸው ታዳጊዎች ትምህርታቸውን እንዳያቋርጦ መርዳት፣ ብሎም ብቁ ዜጋ በሀገሪቱ መተካት፣

ራዕይ

የሀገራችን ወጣት ጤናማ አስተዳደግ እንዲኖረው፣ መልካም ሥነ-ምግባር የተላበሰና እርሱም የሚመሠርተው ቤተሰብ ጽኑ ትውልድ ሆኖ እንዲወጣ መሥራት ነው፡፡

መርሆዎች

• የተግባር ግልፅነት
• በማዕቀፉ ውስጥ የሚያልፍና የሚያገለግል ሁሉ ተጠያቂነት
• ቅልጥፍና እና ውጤታማነት
• የቡድን መንፈስ ማጎልበት
• የሚቻል መሆን ማሳየት
• የግብረ መልስ ጥናት፣ ውጤታ መገምገም
• የስነ-ምግባር ጥናት
• የመማር ልምዶችን ማመቻቸት
• ጠቃሚ ባህላዊ ልምዶች ማዳበር፣